| Song | Sew |
| Artist | Teddy Afro |
| Album | Musica Hiwote: Single Collections, Vol. 1 |
| Download | Image LRC TXT |
| የደመቀው ጀንበር ይጠቁራል በክረምት | |
| እድሜም በወቅት ያልቃል መውደድ በወረት | |
| እውነተኛ አፍቃሪ ማህተቡ ለፅድቅ | |
| ሲኖር አብሮ በልቶ ሲቸገሩ አይርቅ | |
| የበደል አበባ ያበቃላት ለቅሶ | |
| ፍቅር ነኝ ትላለች ደግሞ በርሷም ብሶ | |
| ቢወሻሽ ነው እንጂ አንዱም ላይጎዳ | |
| ምን አሸዋወደ አራዳ ላራዳ | |
| መሰን ተቃርቦ ተይቅር ሎቦ | |
| ሲርቋት ተከታይ ሲላመዷት ባዳ | |
| አትዘልቅ ካንድ ቤት ሁለት ቢላ ለምዳ | |
| አመሏ አይታወቅ ፍዝ ያገነናት | |
| እሳት ሲሏ ውሃ ማር ሲላት እሬት | |
| እንደሰማይ ጀንበር ሁሌ እየደመቀ | |
| ተመልሶ አይወጣም እድሜም ከጠለቀ | |
| ዘመን እያባራ ሁሎ አይኖር ስቆ | |
| ውበትም ይመሻል ጊዜው ጠብቆ | |
| ጀንበር ሲጠልቅ ሲሸሽ ሳቅ ሲተካው ለቅሶ | |
| ያ ያማረው ወራት አይገኝ መልሶ | |
| መወደዷን አውቃ መልኳ ስላማረ | |
| እኮራለሁ ብላ ተረስታ ነበረ | |
| አዝማች | |
| መሄድ መሄድ ያለ ውሎ አዳሩ ጀጅ | |
| እንኳንስ ለወዳጅ ለራሱም አይበጅ | |
| ያንጀት ወዳጅ መስሎ ትልቅ ጉድጓድ ምስ | |
| ንጉሥም ለብልሃት ያበላል ደግሶ | |
| መስቀል ዘ ሰላጢ ከመፅሐፍ ጠቅሳ | |
| እመነኝ አለችኝ ልትቀብረኝ ምሳ | |
| ተምራ ተክና ላሳር ለኩነኔ | |
| ደቁና ስትመጣ ቄስ ሆንኩባት እኔ | |
| ጀንበር ሲጠልቅ ሲሸሽ ሳቅ ሲተካው ለቅሶ | |
| ያ ያማረው ወራት አይገኝ መልሶ | |
| መወደዷን አውቃ መልኳ ስላማረ | |
| እኮራለሁ ብላ ተረስታ ነበረ | |
| እንደሰማይ ጀንበር ሁሌ እየደመቀ | |
| ተመልሶ አይወጣም እድሜም ከጠለቀ | |
| ዘመን እያባራ ሁሎ አይኖር ስቆ | |
| ውበትም ይመሻል ወራትን ጠብቆ | |
| መወሰንን ተቂርቦ ተይቅር ሎቦ |