作词 : RR 作曲 : RR ይገርማል ይገርማል ተርቦ ልብስ ይደርባል ይደንቃል ይደንቃል ተጠምቶ እሳት ይሞቃል ለመናገር መጎምጀቱ ለኛስ ነው ወይ መድኃኒቱ ይገርማል ይገርማል ተርቦ ልብስ ይደርባል ይደንቃል ይደንቃል ተጠምቶ እሳት ይሞቃል ተጠራርተን ከየቤቱ ቃልን መርጠን መሻማቱ 50 ሎሚ ከብዶት ይሸከም ጉልበቴ አታግዙኝ ይቅር ጌጤ ነው ቅርጫቴ ለምን አደንቃለው ጥሩ ቃል መራጩን በምላሱ ስለት የምናብ ቆራጩን ሁላችን ከሆንን የቋንቋ ፈላስፋ በተግባር መስካሪ እማኝ እንዳይጠፋ አንድም ሳይጨበጥ ሳይዳሰስ እንኳን ጀግና ልንባል ነው ቃልን አስተካካይ · M U S I C · ይገርማል ይገርማል ተርቦ ልብስ ይደርባል ይደንቃል ይደንቃል ተጠምቶ እሳት ይሞቃል ተጠራርተን ከየቤቱ ቃልን መርጠን መሻማቱ ይገርማል ይገርማል ተርቦ ልብስ ይደርባል ይደንቃል ይደንቃል ተጠምቶ እሳት ይሞቃል ለመናገር መጎምጀቱ ለኛስ ነው ወይ መድኃኒቱ አስተዋልኩኝ ብሎ የምርም ቢነግረኝ አላጨበጭብም መድሀኒት ካልሰጠኝ ለፈለፈው እንጂ መች አጣሁት እኔ አይራቀቅብኝ ሂድ እላለሁ ያኔ ሁላችን ከሆንን የቋንቋ ፈላስፋ በተግባር መስካሪ እማኝ እንዳይጠፋ አንድም ሳይጨበጥ ሳይዳሰስ እንኳን ጀግና ልንባል ነው ቃልን አስተካካይ ሃምሳ ሎሚ ከብዶት ይሸከም ጉልበቴ አታግዙኝ ይቅር ጌጤ ነው ቅርጫቴ ለምን አደንቃለው ጥሩ ቃል መራጩን በምላሱ ስለት የምናብ ቆራጩን አስተዋልኩኝ ብሎ የምርም ቢነግረኝ አላጨበጭብም መድሀኒት ካልሰጠኝ ለፈለፈው እንጂ መች አጣሁት እኔ አይራቀቅብኝ ሂድ እላለሁ ያኔ